የኢትዮጲያ አየር መንገድ በከፊል አቋርጦ የነበረውን የቻይና በረራ ወደ ሙሉ አቅም በማሳደግ መብረር ሊጀምር ነው።
አየር መንገዱ በእስያ ሀገራት ተጥሎ የነበረው የኮቪድ የጉዞ እገዳ ላላ ማለቱን ተከትሎ ነው ወደ ቻይና የነበረውን በራራ ከፍ ለማድረግ ያቀደው።
ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ አየር መንገዱ ከመንገደኞች ባሻገር የካርጎ አገልገሎትንም በስፋት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።
የኢትዮጲያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዳሉት ቻይና ከአፍሪካ ውጪ የምተገኝ ትልቋ የአየር መንገዱ መዳረሻ ናት ብለዋል።
በሙሉ አቅም የሚጀመረው በረራም ለንግድ፣ ለኢቨስትመንት እና ለሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያግዝ ነው ብለዋል።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-11
