የተባበሩት መንግሳት ያወጣው መረጃ እንዳመላከተው እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 5 ሚሊዮን ሕፃናት በ2021 ዓመት ለሞት ተዳርገዋል።
2.1 ሚሊዮን የሚሆኑ ከ5 እስከ 24 ዓመት የሆናቸውም ከሞት ማምለጥ አልቻሉም።
በትላንትናው ዕለት የወጣው ሪፖርት እንዳመላከተው በ2021 በየ4.4 ሴኮንዶች ከሕፃን እስከ ወጣት ለሞት ይዳረጋሉሉ።
ከዚህም ውስጥ 56 በመቶ የሚሆኑት ሕፃናት ሞት ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት ውስጥ መመዝገቡን ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል።
ድርጅቱ እንዳለው ከሆነ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ የሀገራት ፖሊሲዎች ካልተሻሻሉ በስተቀር እስከ ከ2030 59 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት እና ወጣቶች ለሞት መዳረጋቸው አይቀርም ብሏል።
ወደ 16 ሚሊዮን የሚጠጉት በወሊድ ግዜ የሚሞቱ ናቸው ሲልም አክሏል። ዘገባው የአፍሪካን ኒውስ ነው።
በሳምሶን ገድሉ
2023-01-11
