ሀገሬ ቲቪ

በየዓመቱ 400 ሚሊዮን ሕፃናት ፆታዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል

ኢኮኖሚስት ኢምፓክት ያወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳመላከተው በዓመት 400 ሚሊዮን ሕፃናት ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል።

አንዳንድ ሀገራት በጉዳዩ ላይ ያሳዩት ለዘብተንነት ጥቃቱ የሚደርስባቸውን ሕፃናት ቁጥር እንደቸመረው ተጠቁሟል።

በተለይ በአፍሪካ ሀገራት ሪፖርቶቹ የሚወጡት በሕፃናቱ ላይ ጉዳት ከእረሰ በኋላ መሆኑ የችግሩን ስፋት አመላክቷል።

“Out of the Shadows Global Index 2022” በተሰኘው ሪፖርቱ በጥናቱ ካካተታቸው 60 ሀገራት ውስጥ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ስዊድን ጥቃቱን ለመከላከል ጠንካራ እርምጃ እየወሰዱ ያሉ ሀገራት ናቸው ተብለዋል።

ከአፍሪካ ጠንካራ እርምጃ እየወሰዱ ካሉ 20 ሀገራት መሰለፍ የቻለችው ደቡብ አፍሪካ ብቻ ናት ሲል ዘ ኢስት አፍሪካን ኒውስ አስነብቧል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-01-11