ሀገሬ ቲቪ

ሪፐብሊካኑ በባይደን ላይ ምርመራ እንዲደረግ ፍቃድ ሰጡ

አሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቢሮ የተገኙ ሚስጥራዊ ሰነዶችን የሚፈተሽ ንዑስ ኮኒቴ እንዲቋቋም ፈቃድ ሰጠ።

የተወካዮች ምክር ቤትን የተቆጣጠሩት ሪፐብሊካኑ የዲሞክራቱ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ላይ ጥብቅ ምርመራ እንዲደረግባቸው ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ምርመራውን አሳ የማጥመድ ጉዞም ሲሉ ሰይመውታል።

ሪፐብሊካኖች በአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር፣ የፌደራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) እና ሌሎች የፌደራል ድርጅቶች ምርመራው ላይ እንዲሳተፉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

በጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሪፐብሊካን የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕን እና ካፒቶልን የወረሩትን ደጋፊዎቻቸውን ምርመራ ሲደረግባቸው ሪፕብሊካኑ ተቃውመው እንደነበር ይታወቃል።

በማህሌት አማረ
2023-01-11