ሀገሬ ቲቪ

የስኳር በሽታ መድሃኒት ኢንሱሊን የተገኘበት ቀን

ዘመናዊ ህክምና እምብዛም ባልነበረበት ወቅት የጤናን ጉዳይ በተመለከተ ሰዎች በምን ህመም እንደተጠቁ እና መፍትሄው ምን እንድሆነ እንኳ በቅጡ ሳይረዱ ሞታቸውን መጠባበቅ የግድ ነበር ።

ታዲያ መድሃኒታቸው ሳይታወቁ የብዙ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፉ በሽታዎች መሃከል አንዱ የስኳር በሸታ ነው ።

የስኳር በሽታ መድሃኒት ከመገኘቱ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከ1923 በፊት መፍትሄ የሌለው ገዳይ በሽታ ነው ።

የህክምና ባለሞያዎች በሰኳር በሽታ የተያዘ ታካሚ ሲያጋጠማቸው ህመሙ እንደማይድን እና መፍትሄ እንደሌለው ያስወቁ ነበር ።

በዛሬው ቀን ከ 100 አመት በፊት ታዲያ ይህን በሽታ ለማከም የሚረዳ ኢንሱሊን የተባለ መድሃኒት ለመጅመሪያ ግዜ በሰው ልጆች ላይ ተሞክሮ ወጤታማ መሆን የቻለበት ቀን ነው ።

እንደ ፍረንጆች አቆጣጠር በ1920 ጆርጅ ዋልደን ኢንሱሊን ለስኳር በሽታ እንደ መፈትሄ ለማቅረብ ምርምር ቢጀመርም ኢንሱሊን ለመጀመሪያ ግዜ ለህክምና ተግባር የዋለው በ1923 በ ካናዳ ቶርንቶ ሆስፒታል ወስጥ ነው ።

በካናዳ ቶሮንቶ ሆስፒታል ውስጥ ሊዮናርድ ቶምሰን የተባለ የ14 አመት ልጅ በስኳር በሽታ መያዙ ተነግሮት በሆስፒታል አልጋ ይይዛል ።

በበሆስፒታሉ በህክምና ሰራ እና በኢሱሊን ምርምር ላይ የነበሩት ዶክተር ፍሬድሪክ ባንቲንግ ና የሕክምና ተማሪ የነበረው ቻርልስ ቤስት በላብራርቶሪ ውስጥ ያዘጋጁትን የኢንሱሊን መርፌ ለመጀመሪያ ጊዜ በስኳር ህመም ለተጠቃው የ14 አመት ልጅ ሰጡት። ይሁን እንጂ መድሃኒቱ የቶምሰንን ህመም ከማሻል ይልቅ ከባድ አለርጂ አደረሰበት።

ምርምሩን እየሰሩ የነበሩት የህክምና አባላት ጄምስ ኮሊፕ የተባለ ፋርማሲሲትን ጨምረው ምርምርራቸውን ቀጠሉ ከ 12 ቀናት በኋላ ዳግም በስኳር ህመም ለሚሰቃየው ቶምሰን ሁለትኛውን የኢንሱሊን መርፌ ሰጡት ከዚህ በኋላ የ 14 አመቱ ቶምሰን በደሙ ውስጥ በቂ ኢንሱሊ ማግኘት ቻለ ።

ከዚህ በኋላ ለስኳር በሽታ ኢንሱሊን የተለያዩ ለውጦችን እያደርገ በአሁን ወቅት ከ 400 ሚልየን በላይ ለሚደርሱ የስኳር በሽታ ታካሚዎች መፍትሄ እየሆነ ይገኛል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-11