በሰሜን ሸዋ አንጎለላ ጠራ በሚባል አካባቢ የሚገኘው የአጃማ ጫጫ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት የአማራ ክልል መንግሥት ሊገነባው አቅዶ በ2008ዓ.ም ነበር የመሠረት ድንጋዩ የተጣለው።
በኋላም ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ጋር በተደረገው ስምምነት ጥቅምት 2013 ዓ.ም ላይ ግንባታው ተጀምሯል።
ከልማቱ ጋር ተያይዞ ተነሺ ለሚኾኑ አርሶ አደሮች የካሳ ክፍያ መዘግይት፣ ካሳ ሳይሰጡ አርሶአደሮችን እንዲነሱ መደረጉን የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ተናግረዋል።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ (ዶ/ር) ብርሀኑ መገርሳ የአጃማ ጫጫ ግድብና መስኖ ልማት እና በሌሎች ፕሮጀክት ላይ በተነሳው የካሳ ክፍያ ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ላይ በሰጡት ምላሽ ጉዳዩ ለተቋሙ ከፍተኛ ፈተና መኾኑን ተናገረው ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሳወቁ ተናገረዋል።
በጊዜአዊነት ለካሳ የሚደረጉ ክፍያዎች እንዲቆሙ በገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ መሠጠቱንም ተናግረዋል። እንዲቀርብ ቡድን ተቋቁሞ የካሳ አዋጁ ላይ ምክረ ሀሳብ እየተሰራበት ነው ብለዋል።
የአጃማ ጫጫ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት ሲጀመር 50 ሚሊየን ብር ለካሳ ክፍያ ያስፈልገዋል ተብሎ ነበር አሁን ላይ ግን 2.6 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ነው የተገለጸው።
በልማቱ ተነሺ አርሶአደሮች በ1 ወር ውስጥ ካሳ እንዲያገኙ በሕግ ቢቀመጥም 7 ወር ድረስ ግ ን ሳይከፈላቸው ቆይተዋል ይህ ለምን ኾነ? ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር ብርሀኑ ገንዘብ ከመዓከል እስከ ወረዳው የሚወርድበት አሰራር ረጅም በመኾኑ ነው ብለዋል። በአዋጁ እንዳለው በ 1 ወር ውስጥ ማጥዕናቀቅ ከባድ እንደኾነ ነው የገለጹት።
7 ሺህ ሄክታር በመስኖ ለማልማት ይረዳል የተናለውና 5.32 ቢሊዮን ብር የሚገነባው የአጃማ ጫጫ ግድብና መስኖ ልማት ግንባታው 44% ደርሷል። በጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሏል።
በሙሉጌታ በላይ
2023-01-11
