በኢትዮጵያ ከ 20 እስከ 15 በመቶ የሚሆኑ ጥንዶች በመካንነት የተጠቁ መሆነቸውን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል።
በሃገራችን የሚታየውን የመካንነት ችግር ለመቅረፍ ቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ከአመታት በፊት አገልግሎት ጀምሯል ። ለመሆኑ የመካንነት ችግር መንስኤው ምን ይሆን ።
ዶ/ር ቶማስ
“ በሴቶች ላይ እንቁላሎችን ወደ ማህጸን የሚያስተላልፉ ቱቦዎች ወይም ማህጸን ክፈል በጠባሳ መጎዳት እና እንቁላል የማዘጋጀት ችግር ሲሆኑ ፡፡ በወንዶች ላይ ደግሞ ሰውነታቸው የሚያመርተው የዘር ፍሬ ቁጥር በቂ አለመሆን፣ ወይም የተሰሩት የዘር ፍሬ ቀልጣፋነት ማነስ።በተለያዩ ምክንያቶች (ኢንፈክሽ፣ ጨረር፣ወዘተ) የዘር ፍሬ የሚያፈልቁ ፍሬዎች ሲጎዱ ለመካንነት ችግር መንሳኤ ሊሆኑ ይችላሉ “
የመካንነት ችግር በተፈጥሮ ከእንቁላል ማለቅ እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የመካንነት ችግር ማከም ባይቻልም መፍትሄ ያላቸው የመካንነት ችግሮ አሉ ።
ማዕከሉ የመካንነት ህክምና ለተካሚዎች ለመስጠት የሚጠቀማቸው ለህክምና የሚውሉ ግባቶችን ወጪ በቻ ለመሸፈን በአሁን ወቅት ከ70ሺ ብር ጀምሮ ህክምናውን እየሰጠ ይገኛል ።
ህክምናው ውጭ ሃገር ከ 500ሺ ብር በላይ የሚጠየቅበትም ነው ። ህክምናውን ለማግኘትም ከጎረቤት ሃገራት ጭምር የሚመጡ ታካሚዎች በማእከሉ አገለግሎት እያገኙ ይገኛሉ ።
ማእከሉ እስክ አሁን በሰጠው ህክምና እስከ አሁን ከ 47 በመቶ በላይ ሰኬታማ መሆን የቻለ ሲሆን ይህም ካሉት በአለም አቀፍ መስፈርት የተሻለ አፍጻጸም ነው ተብሏል ።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-12
