ሀገሬ ቲቪ

የፈረንሳይ እና የጀርመን የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ኢትዮጵያ ገቡ

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎንና እንዲሁም የጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኹለቱ ዲፕሎማቶች ጋር ተገናኝተው ውይይት ማድረጋቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

“ጥልቅ እና ፍሬያማ ውይይታችን ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ጋር ያላትን ጠንካራ እና የቆየ ግንኙነትን የሚያንፀባርቅ ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ለውጡን ለማስቀጠል የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-12