ሀገሬ ቲቪ

ቻይና በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ልታደርግ ነው

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት ለደረሰው ጉዳት መልሶ ግንባታ ቻይና ድጋፍ እንደምታደረግ አስታውቃለች።

ከቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አዲሱ የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው ይህን የተናገሩት።

ቻይና ጦርነት በተካሔደባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ እና ለተጎጂ ዜጎች ምግብ፣ ክትባትና ሌሎች ሰብዓዊ እርዳታዎችን እንደላከች ቺን ጋንግ አስታውሰው አሁንም ቢኾን ይህን ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉይ ቃል ገብተዋል።

የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችንም እንደግፋለን ማለታቸውን ሳውዝ ሞኒተሪንግ ፖስት ዘግቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-12