ሀገሬ ቲቪ

በዩጋንዳ የተከሰቶ የነበረው ኢቦላ መቆጣጠር ተቻለ

በዩጋንዳ ለሁለት አስርት አመታት ተከስቶ የነበረው የኢቦላ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ።

የዩጋንዳ የጤና ሚኒስቴር በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በመስከረም ወር ሙቤንዴ በተባለ አካባቢ መታየቱን አስታውሷል።

በሀገሪቱ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ በተሳካ ሁኔታ ተቆጣጥረናል ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ።

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኑም በሃገሪቱ ተከስቶ የነበረውን ወረርሽኝ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት እንደተቆጣጠረችው አስታውቀዋል።

የአለም የጤና ድርጅት መስፈርት በአርባ ሁለት ቀናት ውስጥ ምንም አይነት በበሽታው አዲስ ተጠቂ ከሌለ በሽታውን በቁጥጥር ወስጥ እንደሆነ ይገለጻል ።

በማህሌት አማረ
2023-01-12