ሀገሬ ቲቪ

በደቡብ ሱዳን የተራድኦ ሠራተኞች ተገደሉ

በደቡብ ሱዳን ሦስት የተራድኦ ሰራተኞች በተሰነዘረባቸው ጥቃት መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ።

በታጠቀ ግለሰብ በተሰነዘረ ጥቃት ከሦስቱ የተራድዖ ሰራተኞች ውጪ 11 ንፁሃን ያልታጠቁ ሰዎች መሞታቸውን ዘገባው ጭምሮ አስታውቋል።

በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መግቢያ ላይ ተፈጽሞ በነበረው በዚህ ጥቃት የሞቱት ሦስቱም ደደቡብ ሱዳናውያን የተራድዖ ሰራተኞች ናቸው።

በነዳጅ ዘይት በበለፀገችው አብዬ ግዛት በተፈፀመው ጥቃት ሕፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 14 እንደሆነ ድርጅቱ በሪፖርቱ አመላክቷል።

በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳበት አብዬ ግዛት ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በተባበሩት መንግስታት ጥበቃ ስር ይገኛል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-01-12