ሀገሬ ቲቪ

ለመገንባት የታቀደው የነዳጅ ተርሚናል

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል በጋራ መገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። የነዳጅ ማከማቻው ግንባታ በጂቡቲ ነጻ ወደቦች ቀጠና የሚካሄድ መሆኑን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። የመግባቢያ ስምምነቱ ሃገራቱ ወደፊት በዘርፉ ለሚያካሂዱት ልማትና ግንባታ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ተጨማሪ እድሎችን ለማየት የሚያስችል ነው ተብሏል። ባለፈው የካቲት ወር ላይም የሃገራቱ አየር መንገዶች ፣ የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነጻ ቀጠና እና ወደብ ባለስልጣን እንዲሁም የዶራሌ ደረቅ ጭነት ወደብ አገልግሎት በባህር – አየር ሎጅስቲክስ ላይ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።

በሀገሬ ቲቪ
2022-05-05