ሳውዲ አረቢያ ባላት የዩራኒየም ሀብት የኒውክሌር ኃይል ለማመንጨት ማቀዷን አስታወቀች።
የሀገሪቱ የኃይል ሚኒስትር እንዳሉት በሀገሪቱ የዩራኒየም ክምችት መኖሩን አሰሳዎች እንዳረጋገጡ ጠቁመዋል። ሳውዲ የኒውክሌር ፕሮግራሟን ብሎም የኃይል አማራጯን የማስፋት ዕቅድ አላት።
በ2018 የሀገሪቱ ልዑል ቢን ሳልማን የቀጠናው ጠላታችን ኢራን እንዳደረገችው ሳውዲም የኒውክሌር መሳሪያን ልታመርት ትችላለች ብለው የነበረ ሲሆን አሁን የኒውክሌር ኃይልን በራሴ ዩራኒየም አመርታለሁ ስትል ዕቅዷን አስታውቃለች።
በአብርሃም በለጠ
2023-01-12
