አዲስ የማዕድን አዋጅ በቅርቡ ፀድቆ ወደ ስራ ይገባል ሲል የማዕድን ሚኒስትር ገለፀ።
አዋጁ ከዚህ በፊት የነበረውን የማዕድን አዋጅ ተክቶ በቅርቡ ስራ ላይ ሲውል አጠቃላይ የማዕድን ዘርፉ የሚመራበትን መንገድ እንደሚቀይረው ተገልጿል።
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ አዲሱ አዋጅ የህገወጥ ግብይቱን ለመከላከልም ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል።
12 አመታትን ያስቆጠረው የማዕድን አዋጅ በተለይም በባህላዊ መንገዶች ማዕድን ለሚያወጡ ሰዎች በወረዳ ደረጃ ፍቃድ መስጠት እንዲቻል የሚፈቅድ የነበረ መሆኑ ለህገወጥ የማዕድን ንግድ ትልቅ አስተዋፅዖ አለው ተብሏል።
በማህሌት አማረ
2023-01-13
