የፈረንሳይ እና የጀርመን የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ለ 2 ዓመት የቆየው ጦርነት በሰላም መቋጨቱ የሚደነቅ ውሳኔ ነው አሉ።
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎን እና የጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወሳል።
ሚንስትሮቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ውይይትም አድርገዋል። ጀርመን እና ፈረንሳይ 15.1 ሚሊዮን ዶላር የሚያውጣ ከዩክሬን የተገዛ 50 ሺህ ቶን ስንዴ አስረክበዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።
በሙሉጌታ በላይ
2023-01-13
