
ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሩዋንዳ ስደተኞችን ለፖለቲካዊ ዓላማ ትጠቀማለች ስትል ከሰሰች።
የኮንጎ መንግስት ቃል አቀባይ እንደተናገሩት የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ሃገራቸው ከእንግዲህ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚሰደዱ ሰዎችን አልቀበልም ማለቷን አስታወሰው፣ ይህ ንግግር የሩዋንዳ መንግስት ለሰብአዊነት ያለው ቦታ ዝቅ ያለ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።
ይህንን ተከተሎ ሩዋንዳ ስደተኞችን ለፖለቲካ ፍጆታ እየተጠቀመች ነው ሲሉ ከሰዋል ።
በኮንጎ መንግስት እና በኤም 23 አማፂያን መካከል በተፈጠረውን ግጭት ምክንያት ከ70,000 የሚበልጡ የኮንጎ ዜጎች በሩዋንዳ ተጠልለው ይገኛሉ።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-13