በቻይና የጨረቃ አዲስ አመትን ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ሊስፋፋ ይችላል ሲሉ ተመራማሪዎች አስጠንቅቀዋል ።
የኮቪድ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጨረቃ አዲስ አመትን ለማክበር ብዙ ቻይናዊያን ወደ ትውልድ ስፍራቸው እንደሚጓዙ ተገልጿል።
በዚህም ሳቢያ የጤና አገልግሎት እምብዛም በማይገኝበት በቻይና ገጠራማ አካባቢዎች የኮቪድ ህመምተኞች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲሉ ተመራማሪዎቹ አስጠንቅቀዋል።
የቻይና ኮቪድ ማዕበል በከፍተኛ ደረጃ ከሁለት እስከ ሶስት ወር እንደሚቆይም የቻይና የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል የቀድሞ ኃላፊ ዜንግ ጉዋንግ ተናግረዋል።
በማህሌት አማረ
2023-01-13
