ሀገሬ ቲቪ

ሮቦቱ ጠበቃ

ከቅርብ አመታ ጀምሮ ብቅ እያሉ ያሉ የሮቦት ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የሰውን ልጅ ሰራን በአግባቡ እንዲከወኑ ተደረገው እየተሰሩ ይገኛሉ ።

ለአብነትም በመስተንግዶ፣ እንዲሁም እቃን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር አሁን አሁን ሮቦቶችን መመልከት የተለመደ መጥቷል ።

ከቀናት በፊት ያሆ ኒውስ ይዞት በወጣው መረጃ በታሪክ የመጀመሪያው የሮቦት ጠበቃ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው ሲል አስነበቧል ።

ዱ ኖት ፔይ (DoNotPay) በተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ያበለጸገው የዓለማችን የመጀመሪያው ሮቦት ጠበቃ ከደንበኛው ጋር ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው፡፡

ይህ የሮቦት ሥርዓት ከፍጥነት ገደብ በላይ በማሽከርከር የተከሰሰ ደንበኛውን ነጻ ለማውጣት የሕግ ምክር ሊለግስ በቀጣዩ የካቲት ወር ፍርድ ቤት እንደሚቆም ተገልጿል ፡፡

ሮቦቱን የሰራው ተቋም በበኩሉ ሮቦቱ ዳኛ ፍርድ ቆሞ በአገባቡ የጥብቅንውን ስራ መስራት ይችህላል በሏል ፡፡

በችሎቱ ወቅት ተከሳሹ በፍርድ ቤት በሚኖረው ቆይታ የጠበቃውን ምክር ለመስማት የስማርት ስልክ መተግበሪያ እና የጆሮ ማዳመጫ እንደሚጠቀም ተገልጿል፡፡

በዚህም ሮቦት ጠበቃ በተከሳሹ ስማርት ስልክ ላይ በመሆን ከዐቃቤ ሕግ የሚቀርበውን ክስ እና አስተያየት በመስማት ደንበኛው በክርክሩ ወቅት ምን መመለስ እንዳለበት መመሪያ እንደሚሰጥ ታውቋል ።

የዱ ኖት ፔይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጆሹዋ ብሮውደር ሮቦቱ ይህን ማድረግ የሚያስችለውን አቅም ያገኘው ተጨባጭ የሕግ እውነታዎችን መሠረት አድርጎ በመሠልጠኑ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡

የዱ ኖት ፔይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጆሹዋ ብሮውደር በድርጅታቸው የተሰራው ይህ ሮቦት በፍርድ ቤት በሚያደርገው ክርክር ቢሸነፍ ተከሳሹ ሊደርስበት ለሚችለው ቅጣቶች ለመካስ ቃል ገብተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ጥብቅና የሚቆምለትን ግለሰብ እና ችሎቱ የሚካሄድበትን ፍርድ ቤት ግን ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።

በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-13