ሀገሬ ቲቪ

ከሞተች ሚስቱ ሀውልት ጋር የሚኖረው ባል

መቼም የሚወዱትን ወዳጅ ጓደኛ አሊያም የፍቅር አጋር በሞት ከመነጠል በላይ ጉዳት እና ሕመም የለም። ከወደ ሕንድ ሀገር ሚስታቸውን በሞት ያጡት የ69 ዓመት አዛውንት ያደረጉት ብዙዎችን አስገርሟል።

ታፓስ ሳንዲሊያ ይባለሉ በሕንድ የሚኖሩ እና ከሥራቸው በጡረታ የተሰናበቱ ግለሰብ ናቸው። ከሁለት ዓመት በፊት የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያልታሰበ ሀዘን ቤታቸው እንዲገባ አደረገ። በጣም የሚወዷትን የየ 39 ዓመቷን የትዳር አጋራቸውን በዚሁ ወረርሽኝ ምክንያት ሞት ነጠቃቸው።

ይህን ሀዘን መቋቋም ያልቻሉት ባል። የሚስታቸው ምስል የሚቀርጽላቸው ባለሙያ ፍለጋ አመሩ። እንዳሰቡትም 3 ሺህ ዶላር ወይም ከ 163 ሺህ በላይ ብር በመክፈል ያሰቡትን የሚያሳካላቸው ባለሙያ አገኙ ከ 6 ወራት በኋላም የሟች ሚስታቸውን ቁልጭ ያለ አካላዊ ቅርጽ ያሟላ ቀለል ያለ ሀውልት ማግኘት ቻሉ።

ይህን ሀውልት ታዲያ እንደ ድሮ ሚስታቸው አንድ የቤተሰቡ አባል አድርገው ኑሮአቸውን ቀጥለውዋል።

ከአስር ዓመት በፊት ኢስኪን የተባለውን ቤተ መቅደስ ከባለቤቴ ጋር ስንጎበኝ በሕይወት ያለ የሚመስል የአንድ ሰው ሀውልት አይታ በጣም ተደንቃ ነበር ይላሉ ታፓስ ሳንዲሊያ።

ዛሬ ላይ ደግሞ በሕይወት በነበረችበት ጊዜ እንደተደነቀችበት ዓይነት ምስሏን አሰርቼ የባለቤቴን የመጨረሻ ግብ አሳክቻለሁ ማለታቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ሰላሳ ኪሎ ይመዝናል የተባለው የባለቤታቸውን ሀውልት ሲቀረጽ ከሀውልት ቀራጭ ባለሙያ ጋር በመኾን ሲያግዙ እና ሰሠሩ ነበር። በልጃቸው ሰርግ ላይ ሚስታቸው አድርጋው የነበረው ከሀር የተሸመነ ልብስ ሀውልቱ ለብሷል።

ይህን ሀሳብ ስጠነስሰው በእርግጥ ቤተሰቦቼ ፈቃደኛ አልነበሩም በኋላም ግን ሀሳቤን ተቀብለው ድጋፍም ሲያደርጉልኝ ነበር ብለዋል ታፓስ ሳንዲሊያ።

በሞት የተለዩንን ሰዎች ፎቶ በቤታችን ውስጥ ማስቀመጥ የተለመደ ነው፤ይህን ልምድ ታዲያ ሟችን በሕይወት ያለ የሚያስመስለውን ሀውልት አሰርትን በቤት ውስጥ ብናስቀምጠው ምን ችግር አለው ሲሉም ይሞግታሉ።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-16