ሀገሬ ቲቪ

አልሸባብ ጥቃት በአፍሪካ ህብረት ጦር ሰፈር

የአልሸባብ ታጣቂዎች በሶማሊያ መካከለኛው ሸበሌ ክልል ኤል-ባራፍ መንደር የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ተሰማ። አሸባሪ ቡድኑ ከሁለት ቀናት በፊት የህብረቱን ጦር ሰፈር ወሮ እንደነበር ከአካባቢው ባለስልጣናት እና ከደህንነት ምንጮች ሰምቻለው ሲል ኦል አፍሪካን ኒውስ አስነብቧል። ታጣቂዎቹ ጥቃታቸውን በሁለት አጥፍቶ ጠፊ መኪና ቦምቦች ጀምረው ወደ ጦር ሰፈሩ ገብተዋል ሲሉ የኤል-ባራፍ ከንቲባ አብዱላሂ ሃጂ ሙሁመድ ተናግረዋል። በጥቃቱ ወደ 30 የሚደርሱ የሰላም አስከባሪ አባላት ሳይሞቱ እንዳልቀሩም እየተዘገበ ይገኛል። ወረራዉ በቡሩንዲ ወታደሮች እና በአልሸባብ ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እንዳስነሳም ነው የተዘገበው።

በሀገሬ ቲቪ
2022-05-05