ሀገሬ ቲቪ

የግብጽ እና ቻይና ውይይት

ግብጽ እና ቻይና በቱሪዝም ዘርፍ አብረው ለመሥራት ስምምነት አደረጉ። የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቺንጋንግ በግብጽ ካይሮ ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት እና ከአረብ ሊግ ሸማምንት ጋር ውይይት አድርገዋል።

የቻይና ቱሪዝም በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ማደግ ስለሚችልበት ሁኔታ ውይይት ማድረጋቸውን የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሣሜህ ሽኩሩ ተናገረዋል።

ከዚያ ባለፈ በቀጠናው ስላለው የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ንግግር አድርገናል ብለዋል። ቻይና በግብጽ የምታደርገውን ኢንቨስትመንት አጠናክራ ትቀጥልበታለች መባሉንም አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-16