በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የጥምቀት በዓልን ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።
የጋምቤላ፣ የቤንሻንጉል፣ የደቡብ ሱዳን፣ የቄለምና ምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የከተራ እና የጥምቀት በዓልን በአካባቢዎቹ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲከበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል በቄለምና ምዕራብ ወለጋ በዓሉን በድምቀት ለማክበር የዝግጅት ከሚቴ ተቋቁሞ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በደቡብ ሱዳንም በጁቫ፣ በማላካልና በናስራ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዓሉን ለማክበር ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን እና ወደ አካባቢዎቹም አገልጋዮች መላካቸውን ገልጸዋል።
በአብርሃም በለጠ
2023-01-16
