ሀገሬ ቲቪ

የእስራኤል ባለሙያዎች የስነልቦና ቀውስ ህክምና ስልጠናን በኢትዮጵያ ሰጡ

የእስራኤል የድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎች ለሀገራችን የህክምና ባለሙያዎች የስነ ልቦና ቀውስ ህክምና ልምዳቸውን አካፈሉ።

በስልጠናው ላይ የሀገራችን 26 ዶክተሮች እና ነርሶች መሳተፋቸው ተገልጿል። ስልጠናው በአስፈላጊ አጋዥ መሳሪያዎች የታገዘ መሆኑም ተጠቁሟል።

ስልጠናውን የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር፣ የእስራኤል የጤና ሚኒስቴር እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስተባብረውታል።

በአብርሃም በለጠ
2023-01-16