ሀገሬ ቲቪ

ኦባሳንጆ በሰሜኑ ጦርነት 600 ሺህ ሰዎች ሞተዋል አሉ

በሰሜኑ ጦርነት ከ 600 ሺህ በላይ ዜጎች መሞታቸው እንዳልቀረ የአፍሪካ ህብረት ዋነኛ አደራዳሪ ኦሎሴንጎ ኦባሳንጆ ለፋይናንሻል ታይምስ ገለጹ።

የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ስምምነት በመቋጨቱ በኩል ዋነኛ አደራዳሪ የነበሩት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ በቀን በሺዎች የሚሞቱበትን ጦርነት በፕሪቶሪያ በሰላም ስምምነት እንዲቋጭ ያደረጉት መሪዎች ደስ ሊላቸው ይገባል ብለዋል።

የቤልጂየም ቤንት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሟቾች ቁጥር ከ300 ሺህ እስከ 400 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል ያስታወቁ ሲሆን ሌሎች ደግሞ 300 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠው ነበር።

በአብርሃም በለጠ
2023-01-16