
ቻይና በአፍሪካ የምታከናውናቸው የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ለአህጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት አስተዋፅዖ እንዳለው ተገለፀ።
በ2063 የአፍሪካ ሀገራትን በነጻ ገበያ ለማስተሳሰር ባለመው የአፍሪካ የነጻ ንግድ ቀጠና ውጥን በማገዝ በኩልም አህጉሩን በመንገዶች በማስተሳሰር ቻይና የራሷን አስተዋጽኦ እያበረከተች ትገኛለች ተብሏል።
ቻይና በአፍሪካ ያላት የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ መጠንከሩ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ለአፍሪካ ያላትን ትኩረት ቻይና በአፍሪካ ያላት የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ መጠንከሩ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ለአፍሪካ ያላትን ትኩረት እንደገና በማጤን ወደ አዲስ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ዕቅድን በአፍሪካ ላይ እንድትይዝ እንዳደረጋትም ይታወቃል።
ቻይና በአፍሪካ በምታደርጋቸው የኢንቭስትመንት በሰፊው በትራንስፖርት መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው። በጎርጎሮሳዊያኑ 2063 የአፍሪካ ሀገራትን በነጻ ገበያ ለማስተሳሰር ባለመው የአፍሪካ የነጻ ንግድ ቀጠና ውጥን በማገዝ በኩልም አህጉሩን በመንገዶች በማስተሳሰር ቻይና የራሷን አስተዋጽኦ እያበረከተች ትገኛለች ተብሏል።
ቻይና በቤልት እና ሮድ ኢኒሸቲቭ የአፍሪካን አህጉር በመንገድ የማስተሳሰር እቅዷ መሰረት የኢትዮ-ጅቡቲ 752.7 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ከሃገራቱ ጋር ሰርታ ማጠናቀቋ ለቀጠናው ትልቅ እፎይታን ሰጥቶታል ተብሏል። በዚህም ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ኢትዮጲያ ከግማሽ ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ እቃዎች የተጓጓዙ ሲሆን 47.4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገልጿል።
ቻይና የአፍሪካ ትልቋ የመሰረት ልማት ኢንቨስተር ናት። የቻይና ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ እና የቻይና ልማት ባንክ በአፍሪካ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ከ2007 እስከ 2020 ባለው ግዜ 23 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርገዋል።
ይሄው የቻይና ኢንቨስትመንት ከዓለም ቀዳሚ ስምንት ትልልቅ አበዳሪዎች፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክን ጨምሮ በአፍሪካ መሰረተ ልማት ላይ ኢንቨስት ካደረጉት በ 8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚበልጥ በቻይና እና በአፍሪካ ተኢንቭስትመንት ትብብር ላይ ጥናት ያደረጉት ኢኮኖሚስት አሌክሳንደር አየርቴ ኦዶንኮር ገልፀዋል ።
እንደ ኢኮኖሚስቱ ገለፃ ከጎርጎሮሳውያኑ 2000 ጀምሮ በ20 ዓመታት ውስጥ ቻይና በአፍሪካ 100 ሺህ ኪሜ መንገዶች፣ ከ13 ሺህ ኪሜ በላይ የባቡር መንገዶችን፣ 100 የሚደርሱ ወደቦችን እና 1000 ያክል ድልድዮችን በመስራቱ በኩል ድጋፍ አድርጋለች ብለዋል።
ለአመታት በአሁጉሪቷ የባቡር ሐዲዶች፣ ድልድዮች፣ መንገዶች፣ወደቦች እና የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የገንዘብም ሆነ የሙያ ድጋፍ አድርጋለች፡፡
በአሁጉሪቷ ያለውን የትራንስፖርት እና የመገናኛ መስመሮች እንዲሻሻል እና በአካባቢው ባሉ ሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጎልበት ረገድ ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጓል ያሉት ኦዶንከር
“በግዙፍ የመስረተ ልማት ኢንቨስትመንት ቻይና በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሸቲቯ ከሀገራት እና ቀጠናዎች ጋር በምታደርጋቸው ስምምነቶች በትራንስፖርቱ መሰረተ ልማት ዘርፍ ባላት ከፍተኛ ተሳትፎ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመጣ መነቃቃትን ፈጥራለች” ብለዋል።
ይሄው የቻይና ጠንካራ የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ለአፍሪካ መሰረተ ልማት ግንባታ መኖር ከቅርብ አስርት ዓመታት ወዲህ እያደገ መምጣት የአፍሪካ ቻይና ግንኙነት ይበልጥ እንዲያድግም ምክኒያት ሆኗል።
የቻይና አፍሪካ ወዳጅነትም የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን እና የአህጉሩን ሀገራት በትራንስፖርት መሰረተ ልማት የማገናኘት ሂደትን ለማጠንከር በማገዙ በኩል ጉልህ ሚና አለው መባሉን ሲቲጂኤን ዘግቧል።
በማህሌት አማረ
2023-01-16