ሀገሬ ቲቪ

በ 1.3 ቢሊየን ብር የፓርክ ግንባታ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ የለሚ ፓርክ ግንባታ በይፋ ተጀመረ።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የሚገነባውን ፓርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አስጀምረዋል። ፓርኩ 14 ሺህ 400 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፍ መሆኑ ተመላክቷል።

የፓርኩ ግንባታ በመንግስት እና በግል ባለሀብቶች የሚካሔድ ሲሆን ከ 1 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ታምኖበታል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-17