ሀገሬ ቲቪ

በሰላም ስምምነቱ የተሳሳተ መረጃ ለሚያሰራጨው ማሳሰቢያ ተሰጠ

“ፒስ ፕሮ” የተሰኘው እና በሰላም ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግብረሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የሠላም ሂደት ጠቃሚ ያልሆነ አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠብ የአውሮፓ ሕብረትን አስጠነቀቀ።

ኀብረቱ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም አስተያየት አሊያም ሀሳብ አለኝ ካለ ደግሞ አግባብነት ያለውን መንገድ በመጠቀም ማድረስ ይችላል ብሏል ግብረ ሰናይ ድርጅቱ።

ከዚህ በተጨማሪ የሰላም ስምምነቱን በማመቻቸት ትልቅ ሚና በነበረው የአፍሪካ ኀብረት በኩል አስተያየቱን ሊያደርስ ይገባል ሲል አሳስቧል።

የአውሮፓ ኀብረት በጦርነቱ ወቅት በኢትዮጵያ ጫናዎችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

በማህሌት አማረ
2023-01-17