ሀገሬ ቲቪ

በታንዛኒያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን

መንግስት በታንዛኒያ በእስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ለመመለስ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን በታንዛንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

በኬኒያ በኩል አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለግባት ሲሞክሩ ተይዘው በታንዛኒያና ማላዊ እስር ቤቶች ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ይገኛሉ ተብሏል።

አምስት ሺህ ኢትዮጵያዊያን በታንዛኒያ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው እንደሚኙ የጠቆሙት አምባሳደሩ በተያዘው ዓመት 1 ሺህ 99 የሚሆኑትን ከታንዛኒያ እስር ቤቶች ወደ አገር ቤት መመለሳቸውን ገልጠው ቀሪዎችን ለመመለስም እየተሰራ ነው ብልዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-17