
በኬኒያ ያሉት የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ሀይቆች የውሃ መጠን እየጨመረ መሆኑ ተነገረ።
ከናይቫሻ ሐይቅ አንስቶ እስከ ሶላይ ያሉ ሀይቆች ከ21 በመቶ እስከ 123 በመቶ ድረስ መጠናችው መጨመሩ ነው የተሰማው።
በዚህ ምክያት መኖሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች በጎርፍ እየተጥለቀለቁም ይገኛሉ።
የኬኒያ መንግስት ሪፖርት እንዳደረገው ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ 80 ሺሕ ቤቶች እና 400 ሺሕ ሰዎች በጎርፍ ሳቢያ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ይህ የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ከአፋር ዝቅተኛ ቦታዎች ተነስቶ እስከ ሞዛምቢክ የሚደርስ ነው።
በሳምሶን ገድሉ
2023-01-17