ሀገሬ ቲቪ

የየመንን ሰላም የመመለስ ጥረት

የተባበሩት መንግሥታት የየመን ልዩ መልዕክተኛ ሃንስ ግሩንበርግ በየመን መንግሥት እና በሀውቲ አማጺያን መካከል ሰላም ለማውረድ በሀውቲዎች ቁጥጥር ወደምትገኘው የየመን ዋና ከተማ ሰንአ አቀኑ።

ልዩ መልዕክተኛው የሁለቱን ግጭት በሚያረግቡ ጉዳዮች ላይ ከሁቲ መሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

ውይይቱ በሁቲ በተያዙ አካባቢዎች ለሰራተኞች ተገቢው ደመወዝ እንዲከፈል ፤ የጦር እስረኞችን መፍታትን ጨምሮ ሌሎች ሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

እ.ኤ.አ በ2014 መገባደጃ ላይ በየመን መንግስት እና በሀውቲ አማጺያን መካከል ጦርነት ተቀስቅሶ አማጺያኑ የየመን መንግስትን ከዋና ከተማዋ ሳና ማስወጣቱ ይታወሳል ።

በዮሴፍ ከበደ
2023-01-17