በቻይና የወሊድ ምጣኔ አንስተኛ መሆን ፈተና ሆኗል ተብሏል ።
የቻይና የህዝብ ቁጥር ከስልሳ አመት በኋላ መቀነስ አሳይቷል፡፡ አሁን ላይ ደግሞ የወሊድ ምጣኔው በእጅጉ እየቀነሰ መምጣት አሳሳቢ ሆኗል ተብሏል።
ተንታኞች እንደሚሉት ይህ መቀነስ በቻይና ኢኮኖሚ እድገት ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል ።
የቤጂንግ ብሔራዊ የስታትስቲክስ ቢሮ ይፋ እንዳደረገው መረጃ ከሆነ በ2022 መጨረሻ ላይ የቻይና የህዝብ ቁጥር 1.4 ቢልዮን ገደማ የነበረ ሲሆን ከዚህ ቁጥር 850ሺ የሚኾን መቀነስ ታይቷል ብሏል ።
ቻይና በ1980ዎቹ የሕዝብ ብዛት ቁጥር ለመቆጣጠር የአንድ ልጅ ፖሊሲ ያወጣች ቢሆንም በ2021 ፖሊሲውን አስተካክላ ቤተሰቦች ሦስት ልጆች እንዲወልዱ ፈቃድ ሰጥታለች ።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-17
