ሀገሬ ቲቪ

የ270 ጥንዶች በፍቅር ተጣምሮ የመኖር ሚስጢር

ትዳር የሁለት ሰዎች ጥምረት ብቻ ሳይሆን የሰዎች ረጅሙ የህይውት ጉዟቸው የሚጀምርበት፣ እርስ በእርስ የሚደዳገፉበት ፍሬ የሚያፈሩበት ነው።

አሁን አሁን ላይ ከተጋቢዎች ቁጥር በላይ የፍች ቁጥር በአለም ላይ እየጨመረ ይገኛል። ለዚህም ደግሞ ጥንዶቹ ከትዳር በፊት በደንብ አለመተዋወቅ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣው የግለኝነት ህይወት ተጠቃሽ ናቸው።

ይሄንን ያስተዋሉት በስሜን ቫሌንሺያ ከተማ የተገኙት ቄስ ደግሞ ለዚህ መላ የሚሆን ዘዴ ዘይጃለሁ ይላሉ።

ቄስ ፈርናንዶ ኪዌቫስ ጥንዶችን የማገናኘት ስራቸውን የዛሬ 14 አመት በአንድ ወጣት አነሳሽነት እንደጀመሩት ይናገራሉ።

ሳልቫ የተባለው የካቶሊክ እምነት ተከታይ ወጣት ወደ ቄስ ፈርናዶ ኪዌቫስ በመቅረብ የፍቅር አጋር እንደሚፈልግ እና በቤተክርስቲያኒቷ ከሚመጡ ሴቶች ውስጥ አንዷን እንዲያስተዋውቁት አጥብቆ ይማፀናቸዋል።

እሱም እጅጉን ቀልቡ አርፎባት የነበረችው ወጣት ደግሞ ጊለስን ነበር። ቄሱ ፈርናንዶም ሁለቱን ወጣቶች ያስተዋውቋቸዋል። ይሄ ትውውቃቸው ከአምስት ወራቶች በኋላ ወደ ትዳር ይዘልቃል።

ከዚህም በኋላ በርካታ ሰዎች የትዳር አጋር ፍለጋ መንገዱ ሲጠፋባቸው አስተውያለሁ ብለዋል። የሃይማኖች አባቶችን በዚህ ጉዳይ ላይ ለማማከር የሚደፍሩት ጥቂቶቹ ናቸው ይላሉ ቄስ ፈርናንዶ።

በምዕራቡ ዓለም ማህበረሰብ ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግለኝነት እየበዛ የፍቅር አጋር ለማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን የተገነዘቡት ፈርናንዶ ኩዌቫ ወጣቶችን ለመርዳት ይወስናሉ፡፡

ባለፉት ዓመታት አባ ፈርናንዶ ተስማሚ የሆኑ ጥንዶችን ለማገናኘት ሲሉ ልዩ ቅጽ አዘጋጅተዋል። ሙሉ ስም፣ የእናት ስም፣ ዕድሜ፣ የትውልድ ቀን፣ ቁመት፣ ወቅታዊ ሥራ፣ የትርፍ ጊዜ ልማድ፣ የበጎነት ተሳትፎ፣ ያለቦት ጉድለት፣ የሚፈልጉት የትዳር አጋር መስፈርት እና፣ ለቤተክርስቲያን ያላቸውን ቁርጠኝነት የያዘ ዝርዝር ነው።

ቁመት ወንዱ ከሴቷ መርዘሙና፣ የሚኖሩበት ስፍራ መመሳሰል ለብዙ ትዳር ስኬት ያግዛል የሚሉት ቄሱ እኔ አላማክራቸውም ደግሞም በትዳራቸው ደስተኛ እንደሚሆኑ ቃል አልገባም ስራዬ ማገናኘት ብቻ ነው ሲሉ ይደመጣሉ።

በትዳር ፈላጊዎቹ የተሞሉትን ዝርዝር ባህሪያት እያጤኑ ጥሩ ጥንዶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ላመኑባቸው የእጩ ተጋቢዎቹን ዝርዝር ባህሪያት የተሞላበት ፎርም እና ምስላቸውን ጨምረው ይልካሉ (የሴቷን ለወንዱ፤ የወንዱን ለሴቷ) ። ሁለቱም ከተስማሙም ስልክ ቁጥራቸውን እንዲለዋወጡ በማድረግ የትዳር ጉዞው ይጀመራል።

ይህ ተግባራቸው ታዲያ ላለፉት 14 አመታት 270 ጥንዶችን በትዳር ሲያጣምር አንድም ፍቺ አለማስተናገዱ ዝናቸውን ከስፔን ተሻግሮ እስከ ላቲን አሜሪካ ሀገራት አዝልቆታል።

ለዚህም ደግሞ በትዳር የሚጣመሩት ጥንዶች እምነታቸውን ያልጠበቁ መሆናቸው ለስራቸው እንዳገዛቸው መናገራቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

በማህሌት አማረ
0000-00-00