ሀገሬ ቲቪ

የአሸዋ ቴክኖሎጂ እና የአ.አ. ነጋዴዎች ማህበር ስምምነት

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽን አክስዮን ማህበር እና የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር የከተማዋን የግብይት ስርዓት ለማዘመን እና የሸማቹን ፈተና ለማቅለል ተስማሙ።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ አቅም የሌላቸውን ነጋዴዎችን እና አምራቾች ላይ ትኩረት አድርጌ እየሰራሁ ነው ብሏል።

አሸዋ ቴክኖሎጂ እና የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ለስምምነቱ ተፈጻሚነትም ከሁለቱም ማህበራት የተውጣጡ አባላት ይሰራሉ ብለዋል።

አሸዋ ቴክኖሎጂ አነስተኛ አቅም ያላቸው ነጋዴዎች እና አምራቾችን ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራም አስታውቋል።

ከ2500 በላይ የቨርችዋል ሱቆች ተገልጋዮች እና ከ10 ሺህ በላይ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉትም አስታውቋል።

በአብርሃም በለጠ
2023-01-17