ሀገሬ ቲቪ

9 የቅርጫት ኳስ ሜዳ የሚያክለው ፒዛ

በጣሊያን ሀገር ተጀምሮ አሁን ላይ በበርካታ ሀገራት ተወዳጅነትን ያተረፈ ምግብ ነው ፤ ፒዛ።

ፒዛ በይበልጥም በውጪ ሀገራት የሚዘወተር ቢሆንም ከጊዜያት በኋላ በሀገራችንም በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ ሆኗል ።

ስለ ፒዛ ያነሳንላቹ ያለምክንያት አይደለም ከሰሞኑ አብዛኝዎቻችን የምናቃው በአንድ ትሪ የሚቀርብልን ፒዛ ታይቶ በማይታወቅ መጠን በመሰራቱ የአለምን ክብረወሰን መስበሩን ልንንነግራችሁ ነው ።

ከዚህ በፊት ክብረወሰን የያዘውን የፒዛ መጠን ለመብለጥ አቅዶ የተነሳው ፒዛ ሀት ይህን ግዙፍ ፒዛ ለመስራት 6193 ኪሎ ግራም ዱቄት ፣ ከ3629 ኪሎ ግራም በላይ አይብ ( ቺዝ)፣ 2245 ኪሎ ግራም የቲማቲም ሶስ እና 630 ሺ 496 የተፈጨ የፈረንጅ ቃሪያ የተጠቀመ ሲሆን በነዚህ ግባቶችም ወደ 13990 ካሬ ሜትር የሚጠጋ ፒዛ በመስራት የዓለምን ክብረወሰን ለመስበር ችሏል።

“እንደምታዩት በመጠን በጣም ግዙፍ ነው ። 14 ካሬ ሜትር ይጠጋል ። በአጠቃላይም 68 ሺ ስላይስ ( ተቆራጭ) አለው። የሚያስደስተው ነገር አንድዋም ተቆራጭ አትባክንም ። ከፕሮግራሙ በኋላ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ለሚገኝ ለተቸገሩ ሰወች ምግብ ለሚያበላ ድርጅት እንለግሳለን። በዚህም በጣም ደስተኞች ነን።”

የዚህ ፒዛ መጠን በመተለቁ ጣዕሙ ያን ያህል አይሆንም የሚል ስጋት የነበረ ሲሆን ነገር ግን ተጠናቆ የቀመሱት ሁላ ለመድገም ፍላጎት ያሳዩ እንደነበር ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል ።

ከዚህ ቀደም በ2012 የጣሊያን የምግብ ባለሞያዎች የሰሩት 1261 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ፒዛ የክብረ ወሰኑ ባለቤት የነበረ ሲሆን ፒዛ ሀት ከቀድሞ 12,729 ካሬ በመጨመር ክብረወሰኑን በእጁ አስገብቷል።

በዮሴፍ ከበደ
2023-01-23