የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኬፕ ቬርዴ ገቡ፡፡
አንቶኒዮ ጉቴዝ በአፍሪካ የሚገኙ 10 ደሴቶችን ከአየር ንብረት ቀውስ ለመጠበቅ ውይይት እና የመፈትሄ ሃሳቦችን ለማቅረብ እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ጉቴሬዝ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በኬፕ ቨርዴ የሚገኙ ደሴቶች በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት በሚፈጠረው ቀውስ ግንባር ቀደም ተጎጂ ሆነዋል ብለዋል።
በዚህም በከባድ ድርቅ እና በጎርፍ አድጋ ምክንያት በብዝሃ ህይወት ላይ የመጥፋት አደጋ ተደቅኗል ያሉ ሲሆን የዓለም መሪዎች አስፈላጊውን እርምጃ መወሰድ እንድሚገባቸው አሳስበዋል ።
በጉባኤው የተለያዩ ሃገራት ተሳታፊዎች ይሆናሉ ተበሎም ይጠበቃል።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-23
