
የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ አስተዳደር የፈረንሳይ ወታደሮች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲወጡ አዘዘ።
ወታደራዊ አስተዳደሩ በመቶዎች የሚቆጠሩት የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ነው ያዘዘው።
የሀገሪቱ የዜና አውታር እንደዘገበው ይሄው ውሳኔ በቡርኪናፋሶ ምድር የፈረንሳይ ወታደሮች መኖር መቋጫ ነው ብሏል።
ቡርኪናፋሶ ከሩስያው ዋግነር ግሩፕ ተቀጣሪዎችን የቀጠረች ሲሆን ቀደም ብሎም የጸረ ፈረንሳይ አቋም ያላቸው ተቃሚዎች ከሩስያ ወዳጅነቷን እንድታጠነክር ሲወተውቱ ነበር።
የቀድሞዋ የሀገሪቱ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ ላለፉት 60 ዓመታት ከቡርኪናፋሶ ያላትን ወዳጅነት አስቀጥላለች።
በአብርሃም በለጠ
2023-01-23