ሀገሬ ቲቪ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ መጀመሩ ተገለጸ።

ምክር ቤቱ እያካሄደው ባለው ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች እየመከረ እንደሚገኝና የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ድምጸ ወያነ ዘግቧል።

ከሰሞኑ የትግራይን ክልል የሚያስተዳድረው ሕወሓት፤ የከፍተኛ አመራሮች ለውጥ አድርጓል የሚሉ መረጃዎች ቢወጡም፤ የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በትዊተር በጻፉት መረጃ ሕወሃት አዲስ የክልል ካቢኔ አላዋቀረም ብለዋል፤ በክልሉ የአመራር ሽግሽግ አለመደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይም ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-23