የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።
ውይይታቸው ትኩረቱን የሰላም ስምምነት አፈጻጸሙ ላይ፣ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል የመውጣት ሒደት ላይ እንደነበረም ተሰምቷል።
አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ህብረት የመራውን የሰላም ስምምነት አሜሪካ ለመደገፍ ቁርጠኛ ናት ያሉ ሲሆን የትግራይ ወታደሮች መውጣት የሰሜኑን ክፍል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት አስፈላጊ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ብሊንከን የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ቡድን ምርመራ እንዲያደርግም ሁኔታዎች እንዲመቻቹ አሳስበዋል።
በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ያለው ግጭት ስለሚቋጭበት መንገድ ማውራታቸውንም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ አስታውቋል።
በሙሉጌታ በላይ
2023-01-23
