ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ዩክሬን ለአፍሪካ የግብርና ምርቶችን እያቀረበች ትገኛለች ።
የዩክሬን ፕሬዘዳንት ቮልድሚር ዘለንስኪ በቲወተር ገጻቸው እንዳስታወቁት በድርቅ ለተጋለጡ ኢትዮጵያወያን የሚውል 25ሺ ቶን የሚጠጋ ስንዴ ጁቡቲ ወደ መድረሱን አስታወቀዋል ።
ዩክሬን እስከ አሁን ወደ ኢትዮጲያ ከ 240 ሺ ቶን በላይ ስንዴ ልካለች ። የፈረንጆች አዲስ አመት ከገባ በኋላ ዩክሬን 194 ሺ ቶን የሚጠጋ የግብርና ምርቶችን ለአፍሪካ አድርሳለች ።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-24
