የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አሰባሰብ እና አስተዳደርን ለማዘመን የሚረዳ ዲጂታል የትምህርት መረጃ ሥርዓት ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚንስቴሩ ይህ ያለው በዲጂታል የትምህርት መረጃ ሥርዓት አሰጣጥ ላይ እያደርገ ባለው ውይይት ነው ።
በሚኒስቴሩ የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት እና አይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስብ ለማ እንደገለጹት፣ ዲጂታል ሥርዓቱ ጥራት፣ ተዓማኒነት እና ወቅታዊነት ያለው መረጃን ወጥነት ባለው መልኩ ለማሰባሰብ፣ ለማደራጀት እና ለመተንተን የሚያስችል ነው ብለዋል ።
ለግል እና ለመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካላት በአዲሱ ዲጂታል ሥርዓት አጠቃቀም እና አስተዳር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተስጥቶ ወደ ተግባር መገባቱም ተመላክቷል ።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-24
