የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ደቡብ አፍሪካ ደርሰዋል።
ላቭሪቭ ደርባን ሲደርሱ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ተቀብለዋቸዋል።
ሀገሪቱ የአህጉሪቱ የኃይል ምንጭ ናት ያሉት ላቭሮቭ በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት የምዕራባውያኑን ጎራ ሳትቀላቀል በገለልተኝነት መሟገቷ ይታወሳል።
በሚቀጥለው ወር ደቡብ አፍሪካ ከሩሲያ እና ከቻይና ጋር ወታደራዊ ልምምድ ቀጠሮን ይዛለች።
ከዚህ ወታደራዊ ልምምድ ደቡብ አፍሪካን የሚያስቆም ማንም እንደሌለ ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል።
በሳምሶን ገድሉ
2023-01-24
