ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በኋላ ድፍድፍ ነዳጅ ማምረት እንደምትጀምር የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ። በሶማሌ ክልል ካሉብ እና ኢላላ ባሉ ሁለት የተፈጥሮ ነዳጅ ማውጣት ቁፋሮዎች ስራዎች አሁንም መቀጠላቸው ሲነገር ተጨማሪ የነዳጅ ስፍራዎችን ለማግኘት ጥረት በመደረግ ላይም ይገኛል። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድፍድፍ ነዳጅ ሃብት እንዳላት በጥናት ተረጋግጦ የታወቀው ከ49 ዓመታት በፊት ነው፡፡ ከ6 እስከ 8 ሚሊዮን ትሪሊዮን ሜትር ኩብ የሚደርስ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት እንዳላትም የሚኒስቴሩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ኢትዮጵያ አብላጫውን የኃይል ፍላጎቷን እየሞላች የምትገኘው በከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ ከውጭ በምታስገባው ነዳጅ ነው ኢትዮጵያ ወደ አገር ቤት ከምታስገባቸው የነዳጆች ምርቶች መካከል ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ የአውሮፕላን ነዳጅና ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ዓይነት ናፍጣዎች ናቸው።
በሀገሬ ቲቪ
2022-05-09
