ሀገሬ ቲቪ

ተመራጩ የቻይና የጦር ድሮን

ቻይና የጦር ድሮኖችን በብዛትና በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረቧ በገዥዎች ዘንድ ከሌሎች የድሮን አምራች አገራት አንጻር ተመራጭ አድርጓታል ተብሏል።

በቅርቡ የገቡበትን ጦርነት ድል ለማድረግ ኢትዮጵያን ጨምሮ እንደ ማይናማር፣ ሳውዲ አረብያ እና ኢራቅ ያሉ አገራት የቻይናን የጦር ድሮኖች ምርጫቸው ማድረጋቸውን አልጀዚራ ዝግቧል፡፡

ቻይና ባልፉት አስር ዓመታት ውስጥ ብቻ 282 የጦር ድሮኖችን ለ17 ሀገራት በመሸጥ የዓለም የድሮን ገበያውን እየመራች እንደምትገኝ ስቶክሆልም ኢንተርናሽናል የሰላም ጥናት ተቋም አሳውቋል፡፡

የጦር ድሮኖች የአውደ ውጊያ ሁነትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ይለውጣሉ ብለው የሚያምኑት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አገራቸው ጥራት ያላችውን የጦር ድሮኖች በብዛት ማምረት ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

በዮሴፍ ከበደ
2023-01-24