የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት 2.2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ግምት ያላቸውን መዛግብት እንደተመለከተ የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት እና ዳኛ አቶ ሙሉጌታ አያሌው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኮሚሽኑ 320 መዝገቦች ለውስኔ ተቀጥረው316 መዝገቦች ላይ ውስኔ ሰጥቻለሁ ብሏል። ይህም የእቅዱን 98.7ማሳካት እንደቻለ ነው የተገለጸው።
ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የተቋሙ ደንበኞች በ2 ሚሊዮን ብር የለማ ድረገጽ ስላለው በበይነ መረብ መዝገብ መክፈት የሚችሉበት መንገድ እንደተመቻቸ ተሰምቷል።
ይሁን እንጂ የተጠቃሚው ቁጥር ከ 250 ከፍ እንዳለለ ነው አቶ ሙሉጌታ የተናገሩት።
ዜጎች ከመንግላታት እና በአካል መጥተው መዝገብ ከመክፈት ይህን አመራጭ እንዲጠቀሙም ጠቁመዋል። የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ስድስት ዳኞች ብቻ ያሉ ሲኾን ይህም የችሎት ሒደቱ ላይ መጓተት እንዲመጣ አድርጎታል ተብሏል።
ይህን ችግር ለመቅረፍ በቅርቡ ሌሎች ዳኞች እንደሚጨመሩ አቶ ሙሉጌታ ገልጸዋል።
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን መንግሥት ከፍተኛ የታክስ ክፍያ ጥሎብኛል የሚል ቅሬታ ያላቸው የንግዱ ማኀበረብ ቅሬታቸውን የሚመለከት፣ ነጋዴዎች በጉምሩክና በገቢዎች የተጣሉ ታክሶች ላይ የሚያቀርቡትን ይግባኝ በራሱ ችሎትም የሚመለከት እና ውሳኔ የሚሰጥ ተቋም ነው።
በሙሉጌታ በላይ
2023-01-25
