መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች ንጹሀን በሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ከሰሞኑም ተፈፅመው በነበሩ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች፤ ተገድለዋል ቆስለዋልም።
ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ አርባ_ሺህ ሰዎች ይሞቱብባታል የምትባለው አሜሪካ ከሰሞኑም በካሊፎርኒያ ግዛት በተከታታይ ቀናት ከቤታቸው በሰላም የወጡ ግለሰቦች ባሉበት ቦታ መገደላቸው የዓለምን ትኩረት ስቧል።
የሰሞኑ ጥቃት ሀዘን ሳይወጣ የታጠቀ ግለሰብ በድጋሜ በከፈተው ተኩስም ተጨማሪ ሰባት ሰወች ገድሏል፤ ሌሎች 8 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
ተጎጂዎቹ ሁሉም ቻይና-አሜሪካውያን የእርሻ ሰራተኞች ሲሆኑ ከነጮች የበላይነት ጋር ተያይዞ የተፈጸመ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ ከመሆኑ ከሁለት ቀናት አስቀድሞ በተመሳሳይ ግዛት በታዋቂ የመዝናኛ አዳራሽ የታጠቀ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ 11 ሰወች የተገደሉ ሲሆን የአሁኑ ጥቃት በካሊፎርኒያ ግዛት በስምንት ቀናት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የተፈፀመ የጅምላ ጥቃት መሆኑን ተከትሎ ግዛቲቱ ክፍተኛ ቀውስ ውስጥ ገብታለች።
ጥቃቱ የተፈጸመው ከሳን ፍራንሲስኮ ደቡባዊ ክፍል 50 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ሃፍ ሙን ቤይ ከተማ ውስጥ ከቀናት በፊት በተመሳሳይ ጥቃት ለተገደሉ 11 ሰወች የሀዘን ስነስርዐት እየተኪያሄደ በነበረበት ወቅት ነው።
በስፍራው ተገኝቶ በታጠቀው መሳሪያ የሰባት ንጹሀንን ህይወት የቀጠፈው ዛሆ ቹንሊ የተባለ የ67 ዓመት ዕድሜ ያለው ግለሰብ ሲሆን ጥቃቱን ከፈጸመ ከ 2 ሰዐታት በኋላ በራሱ ተሽከርካሪ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምርቶ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል።
በሀገረ አሜሪካ የመሳሪያ ጥቃቶች ለመበራከቱ ቀዳሚው ምክንያት ሀገሪቱ ጦር መሳሪያ ሽያጭና አጠቃቀም ላይ ያላት ህግ የጠበቀ አለመሆኑ ይነሳል።
የተለያዩ መሪዎች የጦረ መሳሪያዎች እንደማንኛውም ሸቀጥ በሱቁ መቸብቸባቸው አደጋ አለውና ይህ ስርዐት ይሻሻል የሚሉ ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም የሀገሪቱ ኮንግረስ መሳሪያዎችን መሸጥ ከመከልከል ይልቅ ጥቃት አድራሾችን መከላከል ይሻል የሚል ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል።
የሰሞኑ የካሊፎርኒያው ጥቃትም በዚሁ መዘዝ የመጣ ነውና የወቅቱ የአሜካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህን ጥያቄ ዳግም እንዲያነሱ አስገድዷቸዋል ።
በዘፈቀደ በሚሸጡ የጦር መሳሪያዎች አሳዛኝ ክስተቶች እንዲስተናገዱ ማድረጋቸውን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ይህ ጉዳይ እልባት ካልተሰጠው ሀገሪቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደምትወድቅ ተናግረዋል።
ኮንግረሱ የአሜሪካ የጦር መሳሪያ አሻሻጥና አያያዝ ህግን አሻሽሎ እገዳውን በአፋጣኝ ሊያጸድቀው ይገባል ሲሉም በድጋሜ ጠይቀዋል ።
በዮሴፍ ከበደ
2023-01-25
