ሀገሬ ቲቪ

በአንድ ቀን ማየት የቻሉ አንድ ሺሕ ሰዎች

ይህ ታሪክ በእውነተኛ ስሙ ጂሚ ዶናልድሰን፤ በዩቲዩብ ቻናሉ ስሙ ደግሞ ሚስተር ቢስት ይሰኛል።

ይህ ልባም ታዲያ አይነስውርነትን ለመከላከል የሚደረግ ጥረትን 1 ሺሕ ሰዎችን እንዲያዩ በማድረግ አግዟል።

በዓለማችን ላይ ከ200 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቀላሉ ሊታከም በሚችለው በአይን ሞራ ግርዶሽ ሳቢያ ይህቺን አለም ለማየት የታደሉ አይደሉም።

በዓለማችን ላይ ካሉ አይነስውራን መካከል ግማሽ ያህሉ በ10 ደቂቃ ቀዶ ጥገና መመለስ የሚችል እንደሆነም የህክምና ባለሙያዎች ያነሳሉ።

ታዲያ ዶናልድሰን በዓለም ላይ አይነስውርነትን ለመከላከል ከሚሰራው ጊፍት ኦፍ ሳይት ጋር ተገናኘ።

ለህክምና የሚሆን ገንዘብ በማጣታቸው ሳቢያ ለአይነስውርነት ለሚዳረጉ ወገኖች ለመድረስ በመጀመሪያ መመዝገብ ጀመርን የሚሉት የዓይን ቀዶ ጥገና ሐኪም የሆኑት ጄፍ ሌቨንሰን ናቸው።

እሳቸው እንዳሉት ከሆን ታዲያ በአሜሪካ ቤት የሌላቸው የጤና መድህን ሽፋን ያላገኙ ሰዎችን ከተለያየ ቦታ እንደመዘገቡ ይናገራሉ።

ከዚህም በኋላ ለተመዘገቡት ሰዎች ህክምናው ተደረገላቸው፤ ታካሚዎቹም የነበራቸው ስሜት የተለየ ነበር። ዶናልድሰን ሲ ኢንተርናሽናል የተባለ ተቋም በመላው ዓለም መድረስ እንዲችል እንዳደረገው ተናግሯል።

ይህ ተቋም በመላው ዓለም በድምሩ 1 ሺሕ ሰዎችን የዓይን ህክምና በማድረግ ረድቶታል።

ዶናልድሰን በሦስት ሳምንታት ውስጥ ጃማይካ፣ ሆንዱራስ፣ ናሚቢያ፣ ሜክሲኮ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ብራዚል፣ ቬትናም እና ኬንያ ያሉ ታካሚዎች ቀዶ ጥገናውን እንዲያገኙ ማድረግ ችሏል።

ማሕበራዊ መድረክ ለበጎ ዓላማ ሲውል ማለት ይህ አይደል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-01-31