በፓኪስታን ሰሜናዊ ምዕራብ ፔሻዋር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ላይ በደረሰ የአጥፍቶ መጥፋት ፍንዳታ ቢያንስ 83 ሰዎች ሲገደሉ ከ150 በላይ ሰወች መቁሰላቸው ተነገሯል።
ፍንዳታው የደረሰው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ለጸሎት በተሰበሰበበት መስጊድ ዉስጥ መሆኑን የፖሊስ ባለስልጣኑ ሲካንዳር ካን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።
የፖሊስ ባለስልጣኑ አክለውም ህዝባቸው ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በአንድነት እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ጥቃቱን አውግዘው በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በፀሎት ወቅት በፔሻዋር የተፈጸመውን የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት አጥብቀዉን እንደሚያወግዙ ተናግረዋል።ለጥቃቱ እስከአሁን ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም።
በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-31
