ሀገሬ ቲቪ

የሀገራት የሙስና ደረጃ

ሙስና በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ብጥብጥ እያባባሰው ነው ተባለ።

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከሆነ በዓለም ላይ የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ከመቀነስ ይልቅ እየጨመሩ ዓለምን ወደ ባሰ ሁኔታ እየወሰዷት ነው ብሏል።

ተቋሙ በ124 ሀገራት ያለ የሙስና ወንጀሎችን ለክቶ ለሀገራቱ ደረጃ ሰጥቷቸዋል።

ተቋሙ የሙስናን መጠን በለካበት ጥናት ከመካከለኛው ምስራቅ ሊቢያ፣ የመን እና ሶሪያ፤ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ብሩንዲ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ደቡብ ሱዳን የመጨረሻዎቹ 10 ሀገራት ውስጥ ሲገኙ ሶማሊያ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።ሀይቲ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ቬንዝዌላ ሙስና ስር ከሰደደባቸው የመጨረሻዎቹ ደረጃዎች ውስጥ ተካተዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-01-31