ሀገሬ ቲቪ

የምስራቅ አፍሪካ ግጭት መዘዞች

በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ያለው ግጭት እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ረሃብን ፣ መፈናቀልን ብሎም የኑሮ ውድነቱን አስጊ ደረጃ እንዲደርስ ማድረጉ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ፣ በሱዳን፣ እና በደቡብ ሱዳን ከአምስት አመት በታች የሆኑ በርካታ ህጻናት ሥር በሰደደ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ነው ተብሏል። በዚህም በጨቅላ ዕድሜያቸው እየተቀጩ ነው፡፡

የክፍለ አህጉሩ ከእርስበርስ ግጭት በተጨማሪ በአየር ንብረት ለውጥ በተደጋጋሚ ክፉኛ መጎዳቱ የንግድ ልውውጡ እንዲስተጓጎልና ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በዮሴፍ ከበደ
2023-01-31