የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ተመላሽ ብድር ሰብስቤያለሁ አለ፡፡ የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሃንስ አያሌው እንዳሉት ባለፈው ዓመት ከነበረው 40 በመቶ አሁን ወደ 28 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ ተመላሽ ብድሩን መሰብሰብ የተቻለው በተለያየ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩትን ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ በመመለስ ነው፡፡ አሁን ባንኩ ካለው የተመላሸ ብድር በአንድ ዓመት ውስጥ ከ14 በመቶ በታች፣ በሁለት ዓመት ውስጥ ደግሞ ከ10 በመቶ በታች ለማድረስ መታቀዱን ሰምተናል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2022-05-09
